መፃሕፍት
አፍ
የገጽ ብዛት - 254
የመጀመሪያ ሕትመት - 2010 ዓ.ም.
የአዳም ሶስተኛው የረዥም ልብ ወለድ ድርሰት የሆነው 'አፍ' በ 'ቅልልቦሽ' የልጅነት ጨዋታ ቅርፅ የተዋቀረና የአምስት ወጣቶችን ሕይወት የሚተርክ ድርሰት ነው

የስንብት ቀለማት
የገፅ ብዛት - 940
የመጀመሪያ ሕትመት - 2008 ዓ.ም.
ምናልባ ት በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ በርዝመቱ ቀዳሚ የሆነው የስንብት ቀለማት እያንዳንዳቸው በቀለማት ስም በተሰየሙ 8 ዐቢይ ምዕራፎች የተከፈለ የረጀም ልብ ወለድ ሥራ ነው፡፡ መጽሐፉ የአዳም ሦስተኛ የረጅም ልብ ወለድ ሥራ ነው፡፡

መረቅ
የገፅ ብዛት - 604
የመጀመሪያ ሕትመት - 2007 ዓ.ም.
መረቅ ሁለተኛው የአዳም የረጅም ልብ ወለድ ሥራ ነው

ሕማማትና በገና
የገፅ ብዛት - 240
የመጀመሪያ ሕትመት - 2004 ዓ.ም.
ሕማማትና በገና ከ13 ታሪኮች የተሠራ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ ሥራ ነው፡፡

ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ
የገፅ ብዛት - 456
የመጀመሪያ ሕትመት - 2003 ዓ.ም.
በመፅሀፉ የተከካተቱት 8 ታሪኮች 'ከመንግስቱ ነዋይ ጊዜ' እስከ 2075 በምናብ የሚጓዙ ናቸው።
"ምእራፎቹ ገባር የታሪክ ወንዝ ብቻ አይደሉም፡፡ የዘመን ስንጥርጣሪዎችም ናቸው" አለማየሁ ገላጋይ

ከሰማይ የወረደ ፍርፍር
የገፅ ብዛት - 284
የመጀመሪያ ሕትመት - 2002 ዓ.ም.
ከሰማይ የወረደ ፍርፍር አዳም ከ1976-1988 ዓ.ም አዳም በአዲስ አበባ፣ ሆላንድና ካናዳ ሆኖ የፃፋቸው 14 አጫጭር ታሪኮችን በውስጡ የያዘ መድብል ነው፡፡

እቴሜቴ ሎሚ ሽታ
የገጽ ብዛት - 319
የመጀመሪያ ሕትመት - 2001 ዓ.ም.
በዚህ መፅሃፍ ውስጥ የተካተቱት 7 ታሪኮች በብዛት በ1987 ዓም ደራሲው ሆላንድ በነበረበት ጊዜ የተፃፉ ናቸው። ምናባዊ ማጣቀሻ መፃህፍትና ቃላት ያከተተ ሲሆን የመፅሃፉ ርዕስ የሆነው እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ታሪክ ወደ ፊልም ተቀይሮ ለእይታ በቅቷል፡፡

አለንጋና ምስር
የገፅ ብዛት - 356
የመጀመሪያ ሕትመት - 2001 ዓ.ም.
17 አጫጭር ልቦለዶችን አቅፎ የያዘው ይህ መጽሐፍ አዳም በአዲስ አበባ እና በሆላንድ ከ1975-1987 ባለው ጊዜ ውስጥ የደረሳቸውን ታሪኮች ይዟል፡፡ ከእነዚህ አጫጭር ታሪኮች መካከል የድንች መዋስዕት የተሰኘው አጭር ለቦለድ በቤተልሄም አትፊልድ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በሚዩዚካል መልኩ ተቀነባብሮ ቀርቧል፡፡

ግራጫ ቃጭሎች
የገፅ ብዛት - 462
የመጀመሪያ ሕትመት - 1997 ዓ.ም.
መዝገቡ ዱባለ የተሰኘውን ዋና ገጸ ባሕሪ ታሪክ የሚነግረን ይህ መጽሐፍ የአዳም የመጀመሪያ የረጅም ልቦለድ ሥራ ነው፡፡ ሕፅናዊነት የሚባለው የአዳም ልዩ የአጻጻፍ ሥልት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለውም በዚሁ ረጅም ልቦለድ ውስጥ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ማሕሌት
የገፅ ብዛት - 208
የመጀመሪያ ሕትመት - 1981 ዓ.ም.
የአዳም የበኩር ሥራው የሆነው ይህ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ 12 ታሪኮችን ያካትታል፡፡ ከእነዚህም መካከል “ኤልዛቤል” የተሰኘው አጭር ልብ ወለድ በቴሌቪዥን ድራማ መልኩ ተሠርቶ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለዕይታ በቅቷል፡፡

Addis Ababa Noir
(ከሌሎች ደራሲያን ጋር)
የገፅ ብዛት - 256
የመጀመሪያ ሕትመት - 2013 ዓ.ም.
Addis Ababa Noir በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ሲሆን Of Buns and Howls የሚል ርዕስ ያለው የአዳም ረታ ድርሰት ተካቶበታል። ይህ ትረካ አዳም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተመው ብቸኛ አጭር ልብ ወለድ ነው።

አማሌሌ
(ከሌሎች ደራሲያን ጋር)
የገፅ ብዛት - 205
የመጀመሪያ ሕትመት - 2009 ዓ.ም.
አማሌሌ የአጫጭር ልብ-ወለዶች እና ወጎች ስብስብ ሲሆን ዘጠኝ የሚሆኑ ጸሐፍትን ሥራዎች ያካተተ መፅሐፍ ነው። አዳም ረታ የመፅሐፉ ርዕስ ሆኖ የወጣውን “አማሌሌ” የተሰኘ አጭር ልብወለድ አበርክቷል።

አባ ደፋር
(ከሌሎች ደራሲያን ጋር)
የገፅ ብዛት - 200
የመጀመሪያ ሕትመት - 1977 ዓ.ም.
“አባ ደፋር” የተሰኘው የተለያዩ ደራሲያንን አጫጭር ልቦለዶች የያዘው ይህ ስብስብ ሥራ የአዳም ፅሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት የበቃበት መፅሐፍ ነው።
