top of page

ቃለ መጠይቅ: Press
ኦ አዳም!
አዲስ ነገር ጋዜጣ፤
2001 ዓ.ም.
…ለብዙ ወራት ወይም አመታት እንጀራ በወጥ አልበላሁም ነበር። ይታይህ በእንጀራ ነው ያደግኩት። የተገኘው ወጥ ሊኖር ይችላል ጤፍ እንጀራ ግን አለች። ከብዙ ጊዜ በኋላ ታዲያ ጤፍ እንጀራ ሳገኝ ሆዴን የመሙላቱ ነገር አልነበረም አእምሮዬ ያየው። የእንጀራውን ልስላሴ ነበር። መጀመሪያ ያየሁት ኪነቱን ነው። እሱን ስዳብስ ደቂቃዎች አሳለፍኩ። ድሮ በልቼ ብችኮላ የምነሳው (‘እስኪ የበላ ኸው ይርጋ እረፍ’ እንዳልተባልኩ) መብላት ጀምሬ እስከምጨርስ፤ ጨርሼም ከርሞ ስለእንጀራ አንዳንድ ነገር መጠየቅ ጀመርኩ። እንጀራ ምንድን ነው? ለምን ይሄን መሰለ? ለምን ይሄ የምግብ ባህላችን ማዕከል ሆነ? የእንጀራ ባህርይ መልክና ቅርፅ በብዙ ረድፎች ሊተረጎም፣ እናም ጥልቅ የሆነ ትዕምርታዊ እሴት (semiotic value) ሊገኝበት የሚችል ይመስለኛል…

ቃለ መጠይቅ: Welcome
ስለ እንጀራና ስለ መረቅ
ቃለ መጠይቅ: Video
ስለ ብቸኝነት፣ ማህበራዊ ትስስርና መነጠል
ቃለ መጠይቅ: Video
bottom of page